የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር በሶማሌ ክልል የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሰረት መቀመጡን የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳወቁ።
ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ የሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ መሠረት መቀመጡን ይፋ አደርገዋል።
" የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው " ብለዋል።
በሌላ በኩል " የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል " ሲሉ ገልጸዋል።
" እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢንደስትሪ እድገትን ከማሳየት በላይ ናቸው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ " እድሎቻችንን የመጠቀም፣ ትብብሮችን የማጠናከርና ሰላምን የማጽናት የጋራ ኃላፊነታችንን የሚያሳዩ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በኅብረት እና በአንድነት ለእድገት መሰባሰባችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ " ብለዋል።
" ይኽን ስናደርግ እውነተኛውን የኢትዮጵያዊ ማንነት መንፈስ በሚያከብር መንገድ በአለም መድረክ የኢትዮጵያን ስፍራ ከፍ እናደርጋለን " ሲሉ አክለዋል።
Prime Minister Dr. Abiy Ahmed announced that the foundation stone has been laid for a Urea fertilizer factory to be built in the Somali Region through a partnership between Ethiopia Investment Holding and Dangote Group.
In addition, the Prime Minister also announced the groundbreaking of the Gode Oil Refinery, which will be developed by Golden Concord Group.
“The Gode Oil Refinery, by extracting crude oil from the Hilal oil field, refining and processing it, will have a production capacity of 3.5 million tons per year,” he stated.
On the other hand, he explained that “the fertilizer factory, by utilizing gas from the Calub field and a 108-kilometer transport pipeline, will produce and supply 3 million tons annually.”
“These projects go beyond showcasing industrial growth,” said Prime Minister Abiy Ahmed. “They reflect our shared responsibility to utilize our opportunities, strengthen partnerships, and consolidate peace. Therefore, I call upon all Ethiopians to continue uniting in solidarity and togetherness for development.”
He further added, “By doing so, we will elevate Ethiopia’s place on the global stage in a way that honors the true spirit of Ethiopian identity.”
የማዳበሪያ ፋብሪካ መሰረት ተቀመጠ። / The foundation stone for the fertilizer factory has been laid.

Breaking
Breaking
Breaking