ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ቅዳሜ መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል።

በዓሉ ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ፦

- ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ሜክሲኮ፣

- ከወሎ ሠፈር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ፣

- ከቄራ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ ቡልጋሪያ፣

- ከመርካቶ በአቡነ ተ/ኃይማኖት ወደ ጥቁር አንበሳ የሚወስደው መንገድ አቡነ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ፣

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣

- ከአጎና  ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣

- ከሐራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት፣

- ከአዲሱ ገበያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮዲሮማ፣

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ  ቤተ መንግስት አጠገብ፣

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፣

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ እንደሆነ ፖሊስ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ፦
- በ011-1-26-43-59 ፣
- በ011-5-52-63-02/03፣
- በ011-5-52-40-77፣
- በ011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ እንዲሰጥና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
In connection with the Irreecha festival, roads to be closed in Addis Ababa have been officially announced.

The Irreecha Hora Finfinne festival will be celebrated on Saturday, Meskerem 24, 2018 E.C. (October 3, 2025) in Addis Ababa.

The Addis Ababa Police Commission has made public the list of roads that will remain closed until the conclusion of the festival.

Accordingly:

From Mexico Square to Meskel Square (Mexico Road),

From Wollo Sefer to Meskel Square (Olympia Road),

From Kera to Mexico (Bulgaria Road),

From Merkato via Abune Teklehaimanot to Tewodros Square (Abune Teklehaimanot Road),

From St. Urael Square to Meskel Square (Urael Road),

From Bole towards Meskel Square via Olympia (vehicles will be restricted both at the roundabout and underpass, as well as left and right turns),

From Meskel Flower to Olympia (Gazebo Square),

From Agona Cinema to Meskel Square (Tilahune Square, 4th Division),

From Legahar traffic light to Meskel Square (Legahar Road),

From Tele Medhanialem to the Stadium (Tele Road),

From Ras Hotel to the Stadium (Ras Hotel Road),

From Harambe traffic light or Ambassador Cinema to Meskel Square (Harambe Road),

From New Market to Meskel Square (Banko Diro area),

From National Palace to Meskel Square (near the Palace),

From Kazanchis Shell to Bambis (Kazanchis Shell area),

From Jupiter Hotel to ECA (near Bambis Salcot Building).

Starting from Friday, Meskerem 23, 2018 E.C. (October 2, 2025) at 6:00 AM, these roads will remain closed to vehicles until the conclusion of the program, the Addis Ababa Police Commission has announced.

The Police have also stated that stopping vehicles on both sides of the festival area, either for a short or long time, is strictly prohibited.

The public is urged to report any suspicious activities or security concerns through the following phone numbers and to cooperate as needed:

011-1-26-43-59

011-5-52-63-02/03

011-5-52-40-77

011-5-54-36-78 / 011-5-54-36-81

As well as toll-free numbers: 987, 991, and 816.