ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት ባለሃብቶች የሰላም ችግር በስራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን አንስተዋል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ ሰላም በሰጡት ማብራሪያ ባለሃብቶች ጫካ ያሉትን ታጠቂዎች በገንዘብ መደገፍ ወይም ማበረታታት እንዲያቆሙ አሳስበዋል።
ባለሃብቶች እውነተኛ ሰላም ፈላጊ ከሆኑ በጫካ ያሉ ኃይሎችን መደገፍ ፣ መቀለብ አቁመው ወደ ሰላም እንዲመጡ መምከር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
" ሰላም የሚፈልግ ካለ በእኛ በኩል ምንም ችግር የለውም እንቀበላለን እናተ ጫካ ብር አትላኩ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ " መንግስት በሰላም የሚመጡ አካላትን ተቀብሎ ለማወያየት ዝግጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ህግ ማስከበር ስራችን ስለሆነም የሚቀጣ ካለ እንቀጣለን " ሲሉ አክለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሃብታሞች የሀገሪቱን ሰላም በማደፍርስ ላይ 60 በመቶ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ሲሉ ገልጸዋል።
" እየቀለባችሁ ፤ ፋይናንስ እያደረጋችሁ እኔን መልሳችሁ ' ሰላም ' ብትሉኝ አይሆንም። ሰላም ከፈለጋችሁ ፋይናንስ አታድርጉ " ሲሉ አሳስበዋል።
" የሰላም ችግር ትልቅ ኪሳራ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ተቃዋሚዎችም ሆኑ ባለሃብቶች ሰላምን የማረጋገጥ ግዴታ የመንግስት ብቻ አድርገው በመውሰድ ከሃላፊነት መሸሽ ተገቢ አይደለም " ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል መንግስት ኮንትሮባንድን እና ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር ባዘጋጃቸው የፍተሻ ኬላዎች የኮቴ እያሉ ገንዘብ የሚጠይቁ አካላት እንዳሉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ፥ እነዚህ የፍተሻ ኬላዎች የማይኖሩ ከሆነ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች እየገባ የሰዎችን ህይወት እንደሚቀጥፍ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ገንዘብ ሳይጠየቅ ፍተሻ የሚደረግበትን መንገድ ለማመቻቸት መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል፡፡
Minister of Peace Abiy Ahmed (PhD) visited the Nogadu Military Camp and held discussions with the peacekeeping forces.
During this period, the peacekeepers emphasized the importance of peace in their work and expressed their commitment to peacebuilding.
They also stressed the need for comprehensive support for peacekeeping forces, including adequate equipment, training, and the ability to respond effectively to peacekeeping efforts.
"The peace that we seek from you should not be underestimated," said the Peace Minister.
"Ministry of Peace will work towards enhancing the peace and understanding of the peacekeepers," he added.
"The essence of peace is a lasting commitment," said the peacekeepers.
The Minister of Peace will conduct a 60-day assessment of Ethiopia's military camps to address any deficiencies.
"While you are serving, do not forget to say 'peace' to us. Peace is the foundation of all development," he concluded.
However, the peacekeepers emphasized the need for a roadmap to transition from the military camp to the community, under the auspices of the Ministry of Peace, starting from the Nogadu Military Camp.
የኢትዮጵያን ሰላም የሚያናጋው 60% የኢትዮጵያ ሃብታም ነው " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ / "60% of Ethiopia's wealth is what brings peace to Ethiopia." - Prime Minister Abiy Ahmed

Breaking
Breaking
Breaking
Breaking