በቅርቡ የካርኔጊ ሜሎን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ማይክሮሶፍት በጋራ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) በሰዎች የማገናዘብ አቅም ላይ ስለሚኖረዉ ተፅዕኖ አንድ ጥናት (https://www.microsoft.com/en-us/research/wp-content/uploads/2025/01/lee_2025_ai_critical_thinking_survey.pdf) አድርገዉ ነበር።  ይህ ጥናት ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2025 የተካሄደ ሲሆን ባለፈው ሚያዚያ ወር በጃፓን ዮኮሀማ በተካሄደ ኮንፍረንስ ላይ በይፋ ለህዝብ የቀረበ ነው። 319 ሰዎችን ያካተተዉ ይህ ጥናት ስራቸዉ ጥልቅ የሆነ ማሰብን ይጠይቃል የተባሉ ሰዎችን አካቷል። የጥናቱ የተገኙ ግኝቶች ምንድን ናቸው ? በዚህ ጥናት በዋናነት ሶስት ግኝቶች ተቀምጠዋል።  1ኛ. ጥናቱ ከተደረገባቸው ሰዎች አብዛኞቹ ነገሮች ላይ በጥልቀት ማሰብ እና ትኩረት ማድረግ ላይ እንደሚቸገሩ የጥናቱ ውጤት ያሳያል። " የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዉ ይመልሰዋል " ብለዉ ስለሚያስቡ ነገሮችን በጥልቀት የመመርመር ፍላጎት መቀነስም ታይቶባቸዋል። 2ኛ. ከመጠን ያለፈ እምነት በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች ላይ መጣል ሲሆን ጥናቱ የተደረገባቸው ሰዎች ከመሳሪያዉ የሚገኙ ዉጤቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መተማመን እንዳላቸዉ ያሳያል። ውጤቶቹንም እውነተኛነታቸዉን ለማረጋገጥ ሌላ ተጨማሪ ምንጮችን በማየት ለማረጋገጥ እንደማይሞክሩ ውጤቱ ያመለክታል። 3ኛ. የጥናቱ ውጤት ሰዎች ጥልቅ እና የተወሳሰቡ የሚመስሉ ነገሮችን ከማሰብ እና ምክንያታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች የሚወጡ ቀላል እና መሰረታዊ ስህተቶችን በማረም ላይ ያተኩራሉ ብሏል። እንዲሁም የራሳቸዉን አስተሳሰብ በጥቂቱ ስለሚያቀርቡ የግለሰቡን ሀሳብ የማመንጨት ተፈጥሯዊ ብቃቱን እንደሚያሳጣዉ ጥናቱ ይገልጻል። በጥናቱ መሰረት ከመረጃ ጋር የተያያዙ ስራዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል በኋላ መረጃን ከመሰብሰብ ወደ ማረጋገጥ መዞራቸውን ያነሳል። ችግር ፈቺ በሆኑ የሥራ ቦታዎችም ቀጥታ ችግሩን ከመፍታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምክሮቸን ወደመቀበል ዞረዋል ተብሏል። በጥናቱ ከተሳተፉ 319 ሰዎች ውስጥ 83 ያህሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሳሪያዎች ላይ ያላቸው መተማመን የማገናዘብ አቅማቸውን እንዳዳከመው አምነዋል። ከዚህ በተጨማሪ 72 ሰዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያገኙት ምላሽ ስህተት እያለው እንኳን ለማረም እንደማይችሉ በጥናቱ ተመላክቷል። በአጠቃላይ የጥናቱ ማጠቃለያ ሰዎች በስራ ቦታ ላይ ያላቸዉ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች አጠቃቀም የሰዎችን ምክንያታዊ የአስተሳሰብ አቅም እየቀነሰዉ መምጣቱን ያሳያል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ተጠቃሚዎች ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት መሳሪያዎች በሚመነጩ መልሶች ላይ መተማመናቸው ነው። በተጨማሪም ከመተንተን ይልቅ ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት የሚገኙ ውጤቶችን ወደ ማረጋገጥ ፣ ማቀናጀት እና መሰረታዊ ሰህተቶችን ወደ ማረም መዞራቸው መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።
Background:
A recent joint study by Carnegie Mellon University and Microsoft investigated how Artificial Intelligence (AI) tools affect people’s ability to reason and think critically. Conducted between 2024 and 2025, the findings were officially presented in Yokohama, Japan at a conference last April.

The study involved 319 participants—people whose work typically demands deep and critical thinking.

Key Findings (Three Main Conclusions):
1. Decreased Interest in Deep Thinking
Many participants reported struggling to focus or think deeply about complex matters.

A noticeable decline in curiosity and willingness to analyze issues in depth was observed—because people expect AI tools to “think for them.”

2. Over-Reliance and Blind Trust in AI Tools
Participants showed excessive trust in AI-generated results.

They were less likely to verify the output using additional sources.

This overconfidence in AI reduced their inclination to double-check or critically evaluate information.

3. Preference for Simplified Answers
People were more drawn to quick and basic answers from AI rather than forming their own detailed and logical responses.

This trend suggests a reduced ability to generate original ideas or reasoning.

Many participants now rely on AI to the point that it weakens their natural reasoning capabilities.

Additional Data and Observations:
83 out of 319 participants believed their ability to connect ideas had declined due to heavy reliance on AI.

72 participants admitted that even when they noticed errors in AI responses, they felt unable or unwilling to correct them.

Conclusion:
The study concludes that AI tools, especially when overused or blindly trusted, are negatively impacting human reasoning and critical thinking in the workplace.
Rather than collecting, analyzing, and validating information independently, users tend to accept AI outputs without question.

As a result, there's a shift from active problem-solving to passive dependence on AI—especially in situations where humans would typically be required to reason through issues.

Implication:
This highlights the importance of AI literacy, critical thinking education, and maintaining a balance—where AI tools support rather than replace human reasoning.