በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ፤ ነዳጅ እያለ ዋጋ ይጨምራል በሚል እሳቤ ' የለም ' በሚሉ ማደያዎች ላይ  እርምጃ እንደሚወሰድ ገለጹ።

" አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ' ነዳጅ ይጨምራል ' በሚል አገልግሎት አቁመዋል። ነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል።

መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ ከነዳጅ ድጎማ መውጣቱን አመልክተዋል። የነዳጅ ዋጋም በዓለም የነዳጅ ገበያ እንደሚወሰን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ተንቀሳቅሶ እንደተመለከተው በተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች " ቤንዚን የለም ፤ ናፍጣ የለም " የሚሉ ፅሁፎች በብዛት ተለጥፎ አስተውሏል።

ነዳጅ ባለባቸው ማደያዎች ደግሞ ከፍተኛ ሰልፍ ነው ያለው።