ሬድዮ ጣቢያው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።
በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል።
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተለይ ቋሚ ደመወዝተኛው የኑሮ ጫናውን ለመቋቋም እንዲችል የሚቆረጥበት የገቢ ግብር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሻሻልለት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ?
የኢትዮጵያ ብር እና የኬንያ ሽልንግ ከዶላር አንፃር የምንዛሪ ዋጋቸው እኩል ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከ600 ብር ጀምሮ የሚያገኝ ደመወዝተኛ የገቢ ግብር ይቆረጥበታል፤ በኬንያ ደግሞ የገቢ ግብር የሚቆረጠው ከ24,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ደመወዙ 10,900 ብርና ከዚያ በላይ የሆነ ተቀጣሪ 35 በመቶ የገቢ ግብር ሲቆረጥበት፤ በኬንያ ከ800,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው 35 በመቶ የገቢ ግብር የሚቆረጥበት፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል
