የስራ መደቡ ማጠቃለያ፡- የስፖትለስ ጀነራሌ ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ የዴርጅቱ የዕለት ተዕለት ሥራ አመራር፣ አስተዳደር እና ቅንጅት ኃሊፊነት ያለው ቁሌፍ የአመራር ሚና ነው። ዋና ሥራ አስኪያጁ በቀጥታ ለዋና ሥራ አስፈጻሚው ተጠሪ ይሆናል በዋናነት ከፍተኛ የደንበኞችን እርካታና የአሠራር ሌህቀት በማስጠበቅ የጽዳት፣ የጸጥታና የንብረት አስተዳደር አገልግልቶችን በብቃት ለመምራት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ዋና ዋና ኃሊፊነቶች:-
የእለት እለት የተግባር አመራር ስራዎችን ይፈፅማል
የደንበኞች ግንኙነት ስራዎችን ይፈፅማል
የአገልግሎት ጥራት ስራዎችን ይሰራል
የፋይናንስ ስራዎችን መምራት
የገበያ ስራን በትኩረት መስራት
የሚጠበቁ ብቃቶች፡-
በቢዝነስ፣ በአስተዳደር ወይም በተዛማጅ መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው። ወይም ከዛ በላይ ነገር ግን አቅም ፤ ችሎታ፤ተሰጥዎ አለኝ ብሎ የሚያምን በማንኛውም የትምህርት መስክ ዲግሪ ያለው እድል ይሰጠዋል
በአስፈፃሚ አመራር እና በኦፕሬሽን ማኔጅመንት ውስጥ፣ በትክክል በአገልግሎት ኢንደስትሪ ውስጥ የሚታይ ልምድ ያለው እና ቢያንስ 3 ዓመት እና ከዚህ በላይ የስራ ልምድ ያለው።
ችግር ፈቺ እና ውሳኔ የመስጠት ችልታ እንዲኖረው ይጠበቃል።
ጠንካራ የመግባባት ችሎታ ያለው/ያላት
በሁለም የንግድ ግንኙነቶች ውስጥ ከፍተኛ የታማኝነት እና የስነምግባር ደረጃዎችን ለመጠበቅ ቁርጠኝነት ያለው/ያላት
ድርጅቱን በሚገባ መለወጥ እችላለሁ ብሎ የሚያምን/የምታምን
ደሞዝ በስምምነት ሆኑ ኮሚሽን ይኖረዋል
እድሜ ከ30 እስከ 45 አመት
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ ገባ ብሎ ባሻ ወልዴ ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት ስልክ 0908111213 እና 0988190000
ዋና ሥራ አስኪያጅ
